free book gift

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።


Iqra

=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=

ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ


1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።

2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።

3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።

4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
Iqra
Iqra

Homeየወጣቱ ተልዕኮ ምንነትየአቂዳ ትምህርቶችየሶላት መመሪያረመዷንሙስሊም ሴቶችኢስላማዊ ቤተሰብከታሪክ ማህደርሐዲስለወጣቶችትምህርትና መሰረታዊ ክህሎታችጤናችንግጥምጥያቄና መልስኢስላማዊ መዝገበ ቃላት
free book gift

=<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=

ያ ሁሉን በፈጠረው ጌታህ ስም አንብብ!

free book gift

በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው።

free book gift

ጀነትን አስታውስ


በዚህች ህይወት ተርበህ ፣ ደህይተህ ፣ አዝነህ ፣ ታመህ ፣ በደል ደርሶብህ ወይም መብትህ ሳይከበርልህ ቀርቶ ቢሆን በጀነት ውስጥ የሚገኘውን ፀጋ ፣ እረፍት ፣ ደስታ ፣ ሰላምና ዘውታሪነቷን አስታውስ። ይህንን እምነት በውስጥህ ከገነባህ ፤ ለዚያም ስንቅን ለማዘጋጀት ፀንተህ ፣ ጠንክረህ ከሠራህ ኪሳራዎች ሁሉ ወደ ትርፍ ይለወጣሉ ፤ ችግሮችም ወደ ፀጋ ይቀየራሉ። ብልህ ሰዎች ማለት ለማታልቀውና የተሻለች ለሆነችው አኼራ የሚተጉ ናቸው። ከሁሉም ፍጡራን የከፉ ቂሎችና ሞኞች ደግሞ ይህችን ዱንያ ማረፊያቸው ቤታቸውና የዘለዓለም መኖሪያቸው አድርገው የሚያስቡ ናቸው። በመሆኑም ችግሮች ሲደርሱባቸው ቶሎ ተስፋ የሚቆርጡት እነሱ ሆነው ታገኛቸዋለህ ፤ አስከፊ ክስተቶችም ሲያጋጥሟቸው ቶሎ የሚቆጡትም እነሱ ናቸው። ምክኒያቱም ይች ርካሽና ወራዳ ህይወታቸውን እንጂ ሌላ አይታያቸውምና። ይችን አላቂና አጭር ኑሮ እንጂ አይመለከቱም ፤ ከሷ ውጭ ስለ ሌላ ህይወት አያስቡም ፤ ለሷ እንጂ አይለፉም። በመሆኑም ደስታቸው እንዲደፈርስባቸውና ሀሴታቸው እንዲነካባቸው አይፈልጉም። በልባቸው የተደረገውን የድግድግ ግርዶ ቢያነሱ እና ዓይናቸውን የሸፈነባቸውን የድንቁርና ሽፋን ቢያስወግዱ ነፍሶቻቸውን ዘውታሪው የዘልዓለም ህይወት ስላለበት ጀነት የወሯት ነበር። ስለ ፀጋዋ ፣ ሰገነቶቿና ቤቶቿም ያስታውሱ ነበር። አሏህ በራዕዩ ቁርአን ውስጥ ያደረገውን ገለፃ ያዳምጡም ነበር። በአሏህ ይሁንብኝ እርሷ ነች ትኩረት ፣ ትጋትና ድካም የሚሻት።

ለመሆኑ ስለጀነት ሰዎች የተወሳውን አለመታመማቸውን ፣ አለማዘናቸውን ፣ አለመሞታቸውን ፣ ወጣትነታቸው አለመርገፉን ፣ ልብሶቻቸው አለማለቃቸውን ፣ በጥልቅ አስተንትነን አስበናል? ከውስጥ ሆነው ውጫቸው በሚታየውና ከውጭ ሆነው በውስጣቸው በሚታየው ቤቶች ውስጥ እነንደሚኖሩ ፤ በውስጧ ዓይኖች ያላዩአቸው ፣ ጆሮዎች ያልሰሟቸው ፣ በሰዎች ቀልብም ውል ያላሉ ነገሮች የሚበዙበት ፤ ጋላቢ በውስጧ ካሉ ዛፎች የአንዷን ጥላ ተከትሎ ለመቶ አመት ይጓዛል አይጨርሳትም። በውስጧ የድንኴኖች ርዝመት 60 ክንድ ያህላል። ወንዞቿ ረጃጅሞች ናቸው። ሰገነቶቿ ከፍ ያሉ ናቸው። ፍሬዎቿ ቅርቦች ፣ ኩሬዎቿ የሚፈሱ ፣ አልጋዎቿ የተነጠፉ ፣ ደስታዋ የተሟላ ፣ መአዛዋ የሚያውድ ፣ ገፅታዋ የሚያምር የምኞቶች መሟያ ያለባት ናት። ታዲያ ጭንቅላታችን የታለ? ማሰብ አቃተን? ለምን አናስተትንም?

መድረሻው ወደዚህች ጀነት የሆነ ሰው ችግሮቹ ይቅለሉለት ፣ ጉዳት የደረሰባቸውም ዓይኖናቸው ትረፍ። ያጡ የነጡትም ልባቸው ትደሰት። አዋጅ ንቁ እናንተ ድህነት በቀንበሩ የጠመዳችሁ ሰዎች ፣ ረሃብ ያደከማችሁ ፣ ችግሮች የተደራረቡባችሁ የአሏህ ጀነት ውስጥ ትገቡ ዘንድ ጉርብትናውንም ታገኙ ዘንድ መልካም ሥራዎችን አብዙ።

--<({አል-ቁርአን 13:24})>--

«ሰላም ለናንተ ይሁን ፤ ይህ ምንዳ በመታገሳችሁ ነው። የመጨረሻይቱም ሀገር ምን ታምር!»


335

የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
free book gift

Download Islamic Books
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ

Important Web Links


free book gift

free book gift

free book gift

ስለወጣቱ ተልዕኮ ምንነት ለማወቅ እዚህ ላይ ክሊክ ያድርጉ

Copyright©Youth-Mission የወጣቱ ተልዕኮ


Insane